የተቀናጀ የፖስታ ሥራ ማሻሻያ እና የልማት ዕቅድ(IPDP) በኢትዮጵያ ተግባ ራዊ ለማድረግ የተለያዩ ያገባኛል ባዩች የተሳተፉበት የግማሽ ቀን የውይይት መድ ረክ ሐምሌ 21 ቀን 2003 ዓ.ም በመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አዘጋጅ ነት በግዮን ሆቴል ተካሄደ፡፡ በውይይቱ ከተለያዩ የመንግስት አካላት፣ከፖስታ ተቆጣጣሪ፣ ከግል የፖስታ አመላላjc፣ ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት እና ከሌሎች የመንግ ስት ተቋማት የተወጣጡ 54 ተሣታፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክ ኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ፒተር ጋትኮት ለእንግዶቹ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን ፖስታ መረጃን በማስተላለፍ እና ዜጐችን በማቀራረብ ያለው ሚና ከፍተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በተደራሽነቱ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ተጠቃሚ ያደርግ ዘንድ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በዘርፉ የተሰማሩ አካላት እና ያገባኛል ባዮች ድርሻም ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በመሆኑም የፖስታው ዘርፍ አንዱ የመረጃ እና መገናኛ አካል እንደመሆኑ መጠን ዓለም ከደረሰበት የቴክኖሎጂ ዕድገት አንፃር በዓለም ፖስታ ህብረት አለም አቀፍ ቢሮ የተዘጋጀው የተቀናጀ የፖስታ ማሻሻያ እና የልማት ዕቅድ ተግባራዊ ይሆን ዘንድ የሁሉም ያገባኛል ባዮች የተቀናጀ እንቅስቃሴ ወሳኝ መሆኑንም አሳስበዋል፡፡
በዕለቱም በዓለም ፖስታ ህብረት የምዕራብ እና ምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ኘሮጀክቶች አስተባባሪ ሚስስ ግላዲያስ ሙትያቫቪሪ እና የአለም አቀፍ ፖስታ ህብረት አማካሪ ኢም.ሲ.ሞዮ የመወያያ ፅሁፋቸውን ያቀረቡ ሲሆን ሰፊ ውይይትም ተካሂዷል፡፡
በመጨረሻም የደብዳቤ አሰራር የሥራ ሂደት ሥራ አስኪያጅ አቶ በዛብህ አስፋው እንደተናገሩት ቀደም ሲል የፖስታን ተደራሽነት በማስፋት ዜጐችን ተጠቃሚ ከማድረግ አንፃር የተለያዩ እንቅፋቶች ያጋጠሙት እንደነበር ጠቅሰው በቀጣይ አምስት ዓመታት ዘርፉን በማሻሻል ውጤታማ አስተዋፅኦ ለማበርከት የውይይቱ ጠቀሜታ የጐላ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ዘንድ የሁሉም ያገባኛል ባዮች የተቀናጀ እንቅስቃሴ ወሳኝ መሆኑንም አሳስበዋል፡፡
በዕለቱም በዓለም ፖስታ ህብረት የምዕራብ እና ምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ኘሮጀክቶች አስተባባሪ ሚስስ ግላዲያስ ሙትያቫቪሪ እና የአለም አቀፍ ፖስታ ህብረት አማካሪ ኢም.ሲ.ሞዮ የመወያያ ፅሁፋቸ ውን ያቀረቡ ሲሆን ሰፊ ውይይትም ተካሂዷል፡፡ በመጨረሻም የደብዳቤ አሰራር የሥራ ሂደት ሥራ አስኪያጅ አቶ በዛብህ አስፋው እንደተናገሩት ቀደም ሲል የፖስታን ተደራሽነት በማስፋፋት ዜጐችን ተጠቃሚ ከማድረግ አንፃር የተለያዩ እንቅፋቶች ያጋØሙት እንደነበር ጠቅሰው በቀጣይ አምስት ዓመታት ዘርፉን በማሻሻል ውጤታማ አስተዋፅኦ ለማበርከት የውይይቱ ጠቀሜታ የጐላ መሆኑን ጠቁመዋል፡
Jx Latest Commented v2.0
© 2010 Olle Johansson