የመልዕክቱን ክብደት በቅድሚያ ማወቅ ከፈለጉ ይመዝኑ፣
-
መልዕክቱን በግል ፖስታ ወይም ካርቶን በቅድሚያ ማሸግ የተከለከለ ነው፣
-
መልዕክቱ የጉምሩክ ፎርማሊቲ የጤና ጥበቃ ባለሙያ የሚያስፈልገው ከሆነ በቅድሚያ ያሟሉ፣
-
ተሠባሪ ዕቃ ለጊዜው አንልክም የምትልኩ ለሚደርሰው አደጋ ኃላፊነቱን ይውስዳሉ፣
-
ጥራጥሬ እና ያልተፈጨ ቅመማ ቅመም የምትልኩ ደንበኞች የናሙና/Sample/ ፈቃድ ከኮፒ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
-
መልዕክቱ ዶክመንት ከሆነ ፍላየር ኤንቨሎኘ፣ ዕቃ ከሆነ እንደመልዕክቱ መጠን ካርቶን ከማስተናገጃ መስኮት ይረከቡ፣
-
መልዕክቱን ባሉበት ወይም ደውሎ ለማደል ያስችል ዘንድ የሚከተሉትን መረጃዎችን በትክክል ይመዝግቡ፣
-
ጽሁፉ እንዲነበብ አድርገው ይጻፉ፣
-
የተቀባይና የላኪ ሙሉ ስም
-
ውጭ አገር የሚልኩ ከሆነ የመንገድ ስምና የቤት ቁጥር፣ ከተማ እና ሃገር፣
-
አገር ውስጥ የሚልኩ ከሆነ የክፍለ ሃገሩን (ከተማ) ስም በትክክል ይመዝግቡ
-
መልዕክቱን በካርቶን ወይም በኤንቨሎኘ ውስጥ በትክክል ከአስገቡ በኋላ ሳያሽጉ መስኮት ላይ ለሚያስተናግዱ ሠራተኞች ያስረክቡ፣
-
የመላኪያ ዋጋ ይክፈሉ፣ የከፈሉበትን ደረሰኝ ይረከቡ፣